የሲዳማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ
/ Categories: News

የሲዳማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ

የሲዳማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ያካተተ ልዑክ ቡድን በቀን መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡

በልምድ ልውውጡም ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሲዳም ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ፣ የሲዳም ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዘዳንት ዴንጋማ ዲዴ እንዲሁም ዳኞች ተገኝተዋል ፡፡

በእለቱም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት አሰራሮችን የተሻለ ለማድረግ በለውጥ መንገድ ላይ መሆኑን አስገንዝበው እንዲህ አይነት የልምድ ልውውጦች በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረግ የሪፎርም ስራን ወደፊት በማራመድ የፍርድ ቤቶችን የጠበቀ ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ በመሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም አካላት ዝግጁነት ይጠይቃል ብለዋል ፡፡

የፍርድ ቤቶችን አሰራር ከማሻሻልና ከማዘመን አንጻር እየተሰሩ ያሉ አጠቃለይ የፍርድ ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን በተመለከተየተደረሰበትን አሁናዊ ደረጃ የሚያስቃኝ ሰፊ ገለጻ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ገለጻም ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

የሲዳም ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ በበኩላቸው ለልምድ ልውውጡ አመስግነው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በርካታ የለውጥ ሂደቶችን አንደ ማሳያ በመውሰድ የዳኝነትን አገልግሎት ለማዘመን ክልሉ የበኩሉን እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ መሠረተልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡

Previous Article ፍርድ ቤቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የፕሮጀክት ስራ ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ
Next Article የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ
Print
1773