የቅድመ መዋቅር ነባራዊ ሁኔታ ትንተና  እና ረቂቅ ተቋማዊ ለዕላዊ መዋቅር ላይ ውይይት ተካሄደ
/ Categories: News

የቅድመ መዋቅር ነባራዊ ሁኔታ ትንተና  እና ረቂቅ ተቋማዊ ለዕላዊ መዋቅር ላይ ውይይት ተካሄደ

 

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተቋማዊ መዋቅርን እንዲሰራ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት - በፍትህ ፕሮጀክት የተቀጠረ እማካሪ ድርጅት ያካሄደውን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ነባራዊ ሁኔት ትንተና ውጤት በፍርድ ቤቱ በኩል ስራውን እንዲከታተል ለተቋቋመ አብይ ኮሚቴ አቀረበ።

አማካሪ ድርጅቱ ( HST) ቀደም ሲል እያካሄደ ያለውን ጥናት በተደጋጋሚ ለዐብይ ኮሚቴው በማቅረብና የጥናት ስልት፣ ሂደት፣ ይዘት እና ወስን ላይ የማዳበሪያ እና አቅጣጫ ጠቋሚ ሃሳቦችን ሰብስቧል።

ከፍርድ ቤቱ ልዩ ባህሪ እና ስፋት የተነሳ የነባራዊ ሁኔታ ትንተና ረጅም ጊዜ የወሰደ መሆኑ በአማካሪ ድርጅቱ በቀረበ ገለጻ ተጠቁሟል። አማካሪው በዛሬው ገለጻ ከነባራዊ ሁኔታ ትንተና ጋር ተያይዞ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አማራጭ ተቋማዊ ላዕላዊ መዋቅር አቅርቧል።

የዐብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ተኽሊት ይመሰል የመዋቅር ስራው ያልተጠበቀ ረጅም ጊዜ እየወሰድ መሆኑን ገልጸው ከፍርድ ቤቱ ወቅታዊ ፍላጎት አንጻር አማካሪ ድርጅቱ ኃላፊነቱን ልዩ ትኩረት ስጥቶ እንዲሰራ አሳስብዋል።

የኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ክቡር አቶ ተስፋዬ ነዋይ በበኩላቸው በትንተና ውጤቱ ላይ ያላቸውን ምክረ ሃሳብ ስጥተው ላዕላዊ መዋቅሩ እስከ ምድብ ችሎቶች ድረስ ሊኖር የሚገባውን አደረጃጀት ማመልክት እንዳለበት አመላክተዋል።

የፌዴራል ፍርደ ቤቶችን መዋቅር የመቅረጽ ስራ ላዕላዊ መዋቅሩን ተከትሎ የእያንዳንዱ የስራ ክፍል የስራ ፍስት ጥናት፣ የስራ መደብ ትንተና እና ደረጃ ማውጣት፣ የደሞዝ እርከን መተመን እና የጥቅማጥቅም ማዕቀፍ ማዘጋጀት የመሳሰሉት ሰፋፊ ተግባራት የሚቅጥሉ ሲሆን ለእነዚህ ስራዎች መስረት የሆንውን ተቋማዊ መዋቅር በአጭር ጊዜ የማጠናቅቅ አስፈላጊነት ውይይት ተደርጎበታል።

ለአማካሪ ድርጅቱ በኮሚቴው አባላት የተስጡትን ዝርዝር ሃሳቦች በማካተት አና ማሻሻያዎችን በማድረግ ለፌዴራል ፍ/ቤቶች የበላይ አመራሮች ለውሳኔ እንዲያቀርብ የስራ አቅጣጫ ተስጥቷል።

የፍርድ ቤቶችን ተቋማዊ ነጻነት ለማረጋገጥ የአስተዳደር ሰራተኞችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለጠቅላይ ፍ/ቤት በአዋጅ ቁ. 1234 የተሰጥው መሆኑ ይታወቃል። የመዋቅር ስራው ይህንን የአዋጅ ድንጋጌ ከመተግበር ባሻገር የዳኝነት አገልግሎቱን ለማሻሻል ዓላማ ያደረገ ነው።

ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የፌ/ፍ/ቤቶች የአስትዳደር ሰራተኞችን መብትና ጥቅም ጠብቆ  ለማስትዳደር የሚያስችል ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቅርቦ መጽደቁን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

ነጻና ገለልተኛ ፍ/ቤት ለህግ የበላይነት!

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Previous Article የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ፍርድ ቤቱ ከማህበሩ ጋር አብሮ እንደሚሰራ ተገለጸ
Next Article «የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁናዊ ሁኔታ እና የወደፊት ዕይታ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መድረክ ተካሔደ
Print
1970