የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ልዑካን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ
/ Categories: News

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ልዑካን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ልዑካን ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።በጉብኝታቸውም ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ጋር በፍርድ ቤቶች በመከናወን ላይ ስለሚገኙ የለውጥ ስራዎች በተለይም በመልማት ላይ በሚገኙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡ልዑካን ቡድኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ለማስፈን የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ውይይቱን ተከትሎም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰራ ያለውን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ጎብኝተዋል፡፡

Previous Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከኡጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት (ቺፍ ጀስቲስ) ክቡር ሚ/ር አልፎንሴ ኦዊኒ ዶሎ ጋር ተወያዩ፡፡
Next Article ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
Print
894