የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ፡፡
/ Categories: News

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችን እንዲሁም ሌሎች የክልሉን ፍርድ ከፍተኛ አመራሮች ያካተተ ልዑክ ቡድን በቀን 30/12/16 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ልዑክ ቡድኑ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትግበራ እና በመልማት ላይ የሚገኙትን የቴክኖሎጂ መሠረተልማቶች የጎበኙ ሲሆን በተለይም የስማርት ኮርት ሩም አገልግሎት አሰጣጥን፣ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሠረተ ልማት ዳታ ሴንተር እና ኔትዎርክ ኮንትሮል ሩሞችን ተመልክተዋል፡፡

የተቋሙን የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ከተሰሩ ስራዎች ባሻገር ሌሎች የሪፎርም ስራዎች ላይም ገለጻና ውይይትም ተደርጓል፡፡

Previous Article በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በቻይና የዳኝነት ልዑክ ቡድን መካከል የልምምድ ልውውጥ ተደረገ
Next Article ፍርድ ቤቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የፕሮጀክት ስራ ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ
Print
1516