Tuesday, July 22, 2025 / Categories: News የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእውቅና ሽልማት አበረከተ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላደረገው አስተዋጽኦ፣ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ሃላፊና ባለሙያዎች ላደረጉት ድጋፍ የእውቅና ምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡ የእውቅና ምስክር ወረቀቱ የተበረከተው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ከተሟላ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ጋር የተገነቡትን ህንጻዎችን ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡ የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ፣ የዲጅታላይዜሽን መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ የትራንስፎርሜሽን እና ሁሉአቀፍ የለውጥ ስራዎች እንዲሁም የነባር ህንጻ እድሳት እና የአዲስ ማስፋፊያ ግንባታ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚኒስቴር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል እና የክልል ተቋማት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት ሀምሌ14/2017 ተመርቋል። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት በወቅቱ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአጭር ጊዜ ያሳየው እመርታ ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን አንስተው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም የተጠየቀውን ድጋፍ በማድረግ ለስኬቱ ተጋሪ በመሆኑ ደስታው የጋራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም በትብብር መስራት አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያለው ብቻ ሳይሆን የሚያስገኘው ውጤት በስፋትም ሆነ በጥራት የተሻለ በመሆኑ በፌደራልና በክልል መንግሥታት መካከል ያለው ትብብር ይሄን መሠረት ያደረገ ሲሆን ዘርፈ ብዙ መገለጫዎች እንደሚኖሩት አንስተዋል፡፡ Previous Article በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ላይ ለፌደራልና ለክልል የፍትሕ ተቋማት ተሳታፊዎች ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ Next Article የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርባ ምንጭ ማዕከል የህንፃ እድሳት ምርቃት መርሃግብር ተካሄደ Print 656