Tuesday, November 26, 2024 / Categories: News የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገልጋዮች ለፍ/ቤት የሚቀርቡ መዛግብትን ባሉበት አካባቢ ሆነው ማስከፈት የሚችሉበት (e-filing) ሶፍትዌር እና የዳኞች መዝገብ መከታተያ ( judge’s Dashboard) ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገልጋዮች ለፍ/ቤት የሚቀርቡ መዛግብትን ባሉበት አካባቢ ሆነው ማስከፈት የሚችሉበት (e-filing) ሶፍትዌር እና የዳኞች መዝገብ መከታተያ ( judge’s Dashboard) ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ ። በፍርድ ቤቱ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ ስርአት ተቋሙ እያከናቸው ከሚገኘው መጠነ ሰፊ የዲጅታላይዜሽን ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን የተገልጋዮችን እንግልት እና ወጪ የሚቀንስ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር የሚያሰፍኑ እና ለዳኞች ምቹ የስራ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው:: በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ድጋፍ የተዘጋጁት እነዚህ ሁለት ሶፍትዌሮች የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ዓለምአንተ አግደው በተገኙበት ተገምግሟል ። በዚህም ሶፍትዌሮቹ ውስጥ በቀላሉ አዲስ የሚጨመሩ ሂደቶችን ማካተት የሚያስችል በመሆኑ ከፍርድ ቤቱ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ጋር አብሮ ማስማማት የሚያስችል ነው፡፡ ይህን ሶፍትዌር ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ ለዳኞች: ለሬጅስትራሮች: ለችሎት ፀሐፊዎችና ለሌሎች የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና በተለያየ ዙር የሚሰጥ ሲሆን የመጀመሪያ የሙከራ ስራውን በጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የተመረጡ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ በቀጣይም በፍርድ ቤቱ ተግራዊ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የዲጅታላይዜሽን ስራዎች የፍርድ ቤት ስርአቱን እና የተገልጋዮችን እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀይሩ ይሆናል:: Previous Article በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ Next Article በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተዘጋጀ ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ Print 1042