Monday, December 1, 2025 / Categories: News የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ 4ኛውን የአፍሪካ ህገመንግሥታዊ ፍርድ ቤቶች እና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም ‘ህገ መንግሥታዊነት እና ሀገረ መንግሥት ግንባታ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄዱን ተከትሎ የመርሃግብሩ ተሳታፊ እንግዶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል። በቆይታቸውም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን የጎበኙ ሲሆን የፍርድ ቤቱን አበይት የሪፎርም ተግባራት የተመለከተ ገለጻ ቀርቦም ሀሳብ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ተሳታፊ እንግዶቹ ፍርድ ቤቱ ላይ የተተገበሩ እና እየለሙ ያሉት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በሙሉ ሀገር በቀል በሆኑ ተቋማት የተሰሩ መሆናቸው እንዲሁም እየሰጡ ያሉትንም አገልግሎት በእጅጉ አድንቀዋል፡፡ Previous Article ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ ልውውጥ መርሃግብር ተካሄደ Next Article የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የናሚቢያ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ Print 281