የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የናሚቢያ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ
/ Categories: News

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የናሚቢያ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የናሚቢያ ሪፕብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቋማዊ ግንኙነታቸውንና የዳኝነት ስርአታቸውን ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የናሚቢያ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ፒተር ሹቩቴ ናቸው፡፡

የስምምነቱ አላማ በሁለቱ ሀገራት ፍርድ ቤቶች መካከል በሚኖር የጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ መስኮችን በመለየት የትብብር ማዕቀፎችን ለማስፋትና በእነዚህ ማዕቀፎች ላይ የተመሰረተ የጋራ ግብና እሴቶችን ማስቀመጥ ነው፡፡

ስምምነቱ በዋናነት በዲጂታላይዜሽን፣ አቅም ግንባታ፣ የህገመንግስት አተረጓጎም፣ የዳኝነት አስተዳደርና ስትራቴጂያዊ አመራርነትና ሌሎች መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ፍርድ ቤቶች የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ በዳኝነት ስርአቱ ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን በስምምነቱ ላይ በዝርዝር የተመላከቱትን ጉዳዮች ተግባር ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

የናሚቢያ ሪፕብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ፒተር ሹቩቴ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት በማንሳት ይህ ወዳጅነት ከህግ አውጭና ከአስፈጻሚው አልፎ በህግ ተርጓሚውም መካከል ለማጠናከር ይህ ስምምነት ፈር ቀዳጅና ታሪካዊ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራ ፍርድ ቤቶች በጋራ እንዲሰሩና መልካም ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ እድል የሚሰጥ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Previous Article የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ
Next Article የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ የንብረት አገማመት መምሪያዎች/ማኑዋል ላይ ውይይት ተካሄደ
Print
384