Wednesday, February 26, 2025 / Categories: News የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ የልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 18/06/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቴክኖሎጂ አተገባበርና ዲጂታላይዜሽን ሂደት ላይ ዉይይት እና ምልከታ ለማድረግ ነዉ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን አሰራር በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂን በበላይነት እንደሚያስተባብር ተቋም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚያከናዉኗቸዉ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ላይ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በበኩላቸው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የለዉጥ ስራዎችን አድንቀዉ የህዝብ እርካታን ሙሉ በሙሉ ለማምጣት ግን ቀሪ የቤት ስራዎች በመኖራቸው ይህን ለመቅረፍ ዘርፉን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ እና የሰው ኃይሉን በአቅም ግንባታ በማጎልበት ረገድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ ልዑክ ቡድኑም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚኖረው ስኬት ለሌሎች ፍርድ ቤቶችና የፍትህ ተቋማት ዲጂታላይዜሽን ስራዎች አስቻይ ሁኔታዎችን የሚፈጥር በመሆኑ ስራው ተደራሽ እንዲሆንና ቅንጅታዊ አሰራሮች እንዲጠናከሩ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ Previous Article የህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ ፍትህ ሚኒስትር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ Next Article የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የለውጥ ሥራ ተፈጻሚ ለማድረግ የፍርድ ቤቶችን የሰው ኃይል አቅም መገንባት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለጸ Print 812