Monday, January 5, 2026 / Categories: News የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን በቢሮዬ ተቀብዬ፣ በፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ዙሪያ፣ በተለይም የፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ሂደትን በተመለከተ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። በዚህ ውይይት ወቅት፣ የክልላችን ፍርድ ቤቶች በICT ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በቅንጅት እና በትብብር የተጀመሩ መልካም ስራዎች አጠናክረን ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ። ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትም፣ በክልላችን ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን ለማጠናከር የሚያስፈልገውን ድጋፍ ከምንጊዜውም በላይ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጿል። በእኛም በኩል፣ በፍርድ ቤቶቻችን የICT አጠቃቀምን በማጠናከር እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት፣ ከፌዴራል አካላት ጋር በቅንጅት በመስራትና በመደጋገፍ ለህብረተሰባችን የፍትሕ ተደረሽነት ለማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን አድሰናል። ይህም ውጤታማና ተስፋ ሰጪ ውይይት ነበር። በመጨረሻ፣ ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወደ ክልላችን ላደረጉት ጉብኝት ልባዊ ምስጋናዬን ለመቅረብ እወዳለሁ። Previous Article በፍትህ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህጻናትን መብት በማስጠበቅ ሂደት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎችን ሚና ለማጠናከር የሚያግዝ ወርክሾፕ ተካሄደ Next Article የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ Print 166