Friday, December 10, 2021 / Categories: News የክብርት ፕሬዝደንቷ ጉብኝት በድሬደዋ ምድብ ችሎቶች የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎቶችን ጎብኝተዋል:: ክብርት ፕሬዝደንቷ በጉብኝታቸው ከሁለቱም ፍርድ ቤቶች ምድብ ችሎቶች የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ እና የምድብ ችሎቶቹን የችሎት እና የልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን አደረጃጀት ተመልክተዋል፡፡ ከፍርድ ቤቶቹ ክቡራን ዳኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋርም ወይይት አካሄደዋል:: ክብርት ፕሬዝደንት መዓዛ አሸናፊ በውይይታቸው ማጠቃላያ ክቡራን ዳኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች እየሰጡ ለሚገኙት አገልግሎት ምስጋና አቅርበው የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው እንዲሆን ለማድረግ የተጀመሩትን አሰራሮች አጠናክሮ በመተግበር የህዝብ አመኔታ ማትረፍ ይገባል ብለዋል:: ምንጭ፡- የፌ/መ/ደ ፍርድ ቤት እና ፌ/ከ/ፍ/ቤት Previous Article በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በተለያየ መደብና ስራ ክፍሎች ሲከናወን የነበረውን የሬጅስትራር አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከል ሰብሰብ በማድረግ ባለሙያዎች እና ሰራተኞች በቡድን እና በትብብር መርህ ስራቸውን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ Next Article ፍርድ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሴቶችና ሕጻናት ሥርዓተ-ችሎት እንዲዘጋጅ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቆመ Print 1411