Thursday, August 29, 2024 / Categories: News የወንጀል ፍትህ ስርአት ለማሻሻል በሚያስችሉ የትብብር መስኮች ላይ ከስዊድን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ጋር ውይይት ተደረገ የኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ ስርአት ለማሻሻል በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የወንጀል ፍትህ ስርአት ማሻሻያ ፕሮጀክት በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የሚደረገውን የልምድ ልውውጥ ለማሳካት በሚያስችሉና በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ ከስዊድን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ጋር በቀን 22/12/2016 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ውይይት ተደርጓል፡ በውይይቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ በኢትዮጵያ የስዊድን ምክትል አምባሳደር ሄድቪግ ሎም ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የስራ ሃላፊዎችና የአውሮፓ ህብረት ቴክኒካል አሲስታንት ዩኒት ተወካይ የተገኙ ሲሆን የውይይቱ አላማም ፍርድ ቤቶች የወንጀል ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አቅም ለማሳደግና የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮዎች እና ልምዶችን በማጋራት የፍትህ አተገባበሩ የሚያድግበትን መንገድ ለመደገፍ ነው፡፡ የወንጀል ፍትህን አሰፈላጊነት ብሎም በወንጀል ዙሪያ የሚሰሩ አካላትን በእውቀት እና ልምድ የዳበረ ክንውን እንዲያካሂዱ ማድረግ ፍትህን በወንጀል ችሎቶች ላይ የማስተዳደር ስራን ለማሻሻል የሚረዳ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የወንጀል ፍትህ ስርአትን አስመልክቶ ፍ/ቤቱ ከተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ እና የልምድ ልውውጥ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ጠቁመው ስዊድን በወንጀል ነክ ጉዳዮች አስተዳደር ያላት ልምድ እና ተሞክሮ ከማጋራት አኳያ በተለያዪ ደረጃዎች ከፍ/ቤቱ ጋር በቅርበት መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የስዊድን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር በበኩላቸው ስለቀረበው ገለጻ አመስግነው የወንጀል ፍትህ አተገባበር ከማሰደግ አኳያ ላይ ሰፊ እገዛ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን በመግለጽ እገዛው እንዴት እና በምን መልኩ እንደሚደረግ በጥልቀት በማየት እቅዱ ውጤታማ እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ አሳውቀዋል፡፡ ከውይይቱ በተጨማሪም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤትን የዋይድ ኤርያ ኔት ወርክ ዳታ ሴንተርና የስማርት ኮርት ሩሞችን ጎብኝተዋል፡፡ Previous Article የአሜሪካ ኤምባሲ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስማርት ኮርት ሩም የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን አበረከተ Next Article በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በቻይና የዳኝነት ልዑክ ቡድን መካከል የልምምድ ልውውጥ ተደረገ Print 1395