የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ
/ Categories: News

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞችን ያካተተ ልዑክ ቡድን በቀን መስከረም 07 ቀን 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡

በልምድ ልውውጡም ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቦጋለ ፈይሳ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ተገኝተዋል ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንዲህ አይነት ከክልል ፍርድ ቤቶች ጋር በጋራ የሚደረጉ የልምድ ልውውጦች ፍርድ ቤቶች የለውጥ ስራዎች ላይ በቅንጅት እንዲሰሩ በማስቻል በዳኝነት አገልግሎቱ ላይ የተገልጋይ እርካታን ለመጨመርና የዘመነ የዳኝነት አገልግሎትን ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎር ስራዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ ገለጻዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ እንዲሁም የፍርድ ቤትን አሰራር ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ በዲጂታል ስትራቴጂ እየተሰሩ ያሉና ወደፊት ሊሰሩ ስለታሰቡ የለውጥ ስራዎች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቦጋለ ፈይሳ በበኩላቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተሞክሮ ለተቋማቸው ጥሩ ትልቅ ግብአት እንደሚሆን አንስተው የህብረተሰቡን የፍትህ ጥያቄ በተገቢው ለመመለስ አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ብሎም ፍ/ቤቶች ግልጸኝነትን እና ተጠያቂነትን በአማከለ መልኩ እንዲሰሩ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም የልዑክ ቡድኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ መሠረተልማቶችን ጎብኝቷል፡፡

Previous Article የሲዳማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ
Next Article የአሜሪካ ኤምባሲ የዓለም አቀፍ ናርኮቲክስ እና የሕግ ተፈጻሚነት ቢሮ ልኡክ ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ጋር የአጋርነት ውይይት አካሄደ
Print
188