የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ሲያደርጉ የነበረው ጉብኝት እና ውይይት ተጠናቀቀ
/ Categories: News

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ሲያደርጉ የነበረው ጉብኝት እና ውይይት ተጠናቀቀ

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተዘረጉ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች እና የለሙ የተለያዩ መተግበሪያዎች ምልከታ ያደረጉ ሲሆን ከፍርድ ቤቱ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ክቡራን ዳኞቹም ባደረጉት ምልከታ እየተሰሩ ላሉ የቴክኖሎጂ ሪፎርሞች ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ ሀሳብ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

ጉብኝቱ በትግበራ ወቅት በቀላሉ ወደ ስራ ለመግባት የሚያግዝ በመሆኑ መሰል ጉብኝቶች እና ውይይቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል፡፡

Previous Article ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሪጅስትራሮች ሲሰጥ የነበረዉ የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ
Next Article የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጸደቀ
Print
469