Friday, June 14, 2024 / Categories: News የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/13 እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/13 እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር .1233/13 እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13ን ለማሻሻል የሚያስችል የግብዓት ማሰባሰብ የውይይት መድረክ ከዉጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ/ም አከናዉኗል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሁለቱም አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ፀድቀው ስራ ላይ ከዋሉ ብዙ እድሜ ያስቆጠሩ ባይሆንም በፌደራል ፍርድ ቤቶች ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት በእቅድ ተይዘው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ሁለቱን አዋጆች ማሻሻል እንደሚገኝበት እና የማሻሻል ሂደቱም በአዋጆቹ ላይ በትግበራ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን እንዲሁም በህጉ እንደ አዲስ መካተት ያለባቸውን ሃሳቦች በዳሰሳ በመለየት የተጀመረ መሆኑን ገልፀዋል የአዋጆቹ መሻሻል የፌዴራል የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ለማስጠበቅ፣ የተጠናከረ የተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት እና በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም እንዲሁም ከተቋሙ ሁለንተናዊ ለውጥ ጋር የሚሄዱ አሰራሮች እና አደረጃጀቶች የህግ መሠረት እንዲኖራቸው በማስቻል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ከባለድርሻ አካላት የሚገኘዉ ሃሳብ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎውሽፕ ፕሬዝደንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ በበኩላቸው አዋጆቹ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በደኝነት ስርዓቱ ያለውን ሚና በግልፅ በሚያሳይ እና በፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች በሚያግዝ መልኩ መሻሻል ያለባቸውን ጠቁመዉ ለዚህ መሳካት ድርጅታቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ በቀን 17/09/2016 ዓ.ም በሶስቱም ደረጃ ከሚገኙ የፍ/ቤት አመራሮች፣ ዳኞችና የስራ ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት መደረጉ የሚታወስ ነው:: Previous Article የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/13 እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13ን ለማሻሻል የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጀ Next Article የፌደራል ፍትህ አካላት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር አብይ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ተካሄደ Print 444