የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ
/ Categories: News

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

የጉባዔው ጽ/ቤት እንደገለጸው የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ምርመራ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለጉባዔው ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተወያይቶ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34(2) መሰረት የሁለቱንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኗል፡፡

ምንጭ፡- የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ

Previous Article ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘመነ
Next Article ዳኞች ስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ የጽሁፍ ውጤቶችን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
Print
249