Monday, November 17, 2025 / Categories: News የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን ላይቭስ በሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት አስተባባሪነት የተሰበሰቡ መጽሃፍቶችን ተረከበ ሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን ላይቭስ በመባል የሚጠራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ቡክስ ፎር አፍሪካና ቶምሰን ሪዉተርስ ከሚባሉ ለጋሽ ድርጅቶች ለትምህርት ቤቶች እና ለፍትህ ተቋማት የሚያገለግሉ መጻሃፍቶችን በማሰባሰብ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ አድርጓል፡፡ የሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን ላይቭስ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ጸሃይ ወዳጆ እነዚህ በድጋፍ መልክ የተገኙና 483,900 ዶላር ዋጋ ያላቸዉን መጽሃፍቶች ከለጋሽ ድርጅቶች እንዲሰበሰቡ በማድረግና ወጪያቸዉ ተሸፍኖ ወደ ኢትዮጵያ እንዲላኩ አድርገዋል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ መጽሃፍቶች ለትምህርት ቤቶች የተላኩ ሲሆን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለፌዴራል ህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አነስተኛ ቁጥር ያላቸዉ የህግ መጽሃፍቶች እንዲደርሳቸዉ ተደርጓል፡፡ መፅሃፍቶቹ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ሁሉንም አካላት በመወከል ሲያስተባብር የነበረው የፌዴራል ጠቅላፍ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ መጽሃፍቶች ከለጋሽ ድርጅቶች እንዲሰበሰቡ እና ወጪያቸዉ ተሸፍኖ ወደ ኢትዮጵያ እንዲላኩ ያደረጉትን ወ/ሮ ጸሃይ ወዳጆን፣ መጽሃፍቶቹ ከቀረጥ ነጻ ሆነው እንዲገቡ ባለዉ መመሪያ መሰረት ፈቃድ የሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ እና የማጓጓዝ ሂደቶች እንዲሳለጡ ያደረጉ የጉሙሩክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት እንዲሁም የአገር ውስጥ የማጓጓዝ ወጪን በመሸፈን ትብብር ያደረገዉ የፌዴራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩትን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ Previous Article በአስማሚነት ክህሎት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረዉ የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ Next Article የተግባር ልምምድ (ስልጠና) በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እየተሰጠ ይገኛል Print 444