Thursday, July 18, 2024 / Categories: News, CJPO NEWS የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ ፍርድ ቤቱን በመወከል ገለጻ ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳኛ ተክለሐይማኖት ዳኜ ሲሆኑ ፍርድ ቤቶች የህጻናትን መብት እና ጥቅም ትርጉም ባለው መልኩ ለማስጠበቅ እንዲረዳ መመሪያዎችን በማውጣት፣ለህጻናት ተስማሚ ፍርድ ቤቶችን በማደራጀት፣ነጻ የህግ እና ማህበራዊ ሳይንስ ድጋፍ በመስጠት፣የዳኞችን አቅም በማሳደግ፣አባትነትን በዘረ-መል ምርመራ በማረጋገጥ ፣ በወንጀል ነክ ጉዳይ ገብተው የተገኙ ህጻናት አገልግሎት በማሻሻል እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ የወርክሾፑ ተሳታፊዎች በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመገኘት የህጻናት የህግ ከለላ ማዕከልን እንዲሁም ለህጻናት ተስማሚ ችሎትን ጎብኝተዋል፡፡ Previous Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ክትትልና ግምገማ ተካሄደ Next Article ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተከላካይ ጠበቆች ፣ረዳት ዳኞች እና ሬጂስትራሮች ስልጠና ተሰጠ Print 2654