Friday, February 13, 2026 / Categories: News የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፍርድ ቤቶች አሰራርን እና የሰበር ውሳኔዎች ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት(MOU) በቀን 05/06/2018 ዓ.ም ተፈራርሙ የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ አላማ ህብረተሰቡ የህግ ጉዳይን በተመለከተ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ በሚያስችል መልኩ የፍርድ ቤቱን ውሳኔዎችና በተገልጋዮች ላይ ተፈጻሚነት ያላቸውን የተለያዩ አሰራሮች፣ መመሪያዎች እና መረጃዎችን በሚዲያ አማራጭ ተደራሽ ለማድረግ ነው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ስምምነቱ በንቃተ ህግ ረገድ የሚሰራዉን ስራ አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚያሳድገው ያላቸውን እምነት ገልፀው በተለይም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጡ የሰበር ዉሳኔዎች ከተወሰኑበት ቀን ጀምረዉ አስገዳጅነት ያላቸው በመሆናቸዉ ለህብረተሰቡ በፍጥነት ተደራሽ መሆን እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ አያይዘውም የፍ/ቤቱን አሰራር ከማስተዋወቅ ባለፈ የህብረተሰቡን የህግ ንቃተ ህሊና ከፍ ከማድረግ አንጻር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በመላዉ ሀገሪቱ ካለው ተደራሽነት አንጻር ስምምነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ በበኩላቸው ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱ የፍርድ ቤቶችን አሰራሮችና መረጃዎች ከማስተዋወቅ ባለፈ የህብረተሰቡን የህግ ንቃተ ህሊና ከፍ ለማድረግ የሚያግዝ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ጅማሮ መሆኑን እና በፍርደ ቤቱ እና በኢቢሲ በኩል የሚከናወኑ ተግባራት ላይም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ Previous Article በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ ተካሂዷል። Next Article ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ስልጠና ተሰጠ Print 372