የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ጋር በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች ተወያዩ
/ Categories: News

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ጋር በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች ተወያዩ

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) የፈረንጆቹ 2025 እየተገባደደ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ ከፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው ሁኔታዎች ከፍርድ ቤቱ አመራሮች ጋር በቀን 23/03/2018 ዓ.ም ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም የፌደራል ክልል ግንኙነትን ከማጠናከር አኳያ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ላለፉት አመታት ከፍርድ ቤቱ ጋር በአጋርነት በመስራት የዳኝነት አካሉ እንዲጠናከር በበጀት፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች ላይ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን ሲወጣ መቆየቱን በማንሳት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ተጠሪ ሳሙኤል ዶኦ (ዶ/ር) በበኩላቸው የህግ የበላይነት መከበር ዜጎች በፍርድ ቤት ላይ ያላቸው እምነት አንዲጨምርና እንደ ሀገርም የተረጋጋ ሰላም እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ በመሆኑ ይህንን እውን ለማድረግና ፍርድ ቤቶች የጀመሩት የሪፎርም ጉዞ የተሳካ እንዲሆን የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) በ2025 ላደረገው ድጋፍና አጋርነት ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

Previous Article የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ የንብረት አገማመት መምሪያዎች/ማኑዋል ላይ ውይይት ተካሄደ
Next Article የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልወውጥ አደረጉ
Print
584