የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ስራዎችን በይፋ አስጀመሩ
/ Categories: News

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ስራዎችን በይፋ አስጀመሩ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቪድዮ ኮንፍረንስ፣በሶማሊኛ ቋንቋ የሚሰራ የመዝገብ አስተዳደር፣ የኢፋይሊንግ አገልግሎት እንዲሁም የቀጠሮ መከታተያ አገልግሎትን በቀን 12/02/2018 ዓ.ም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክቡራን ፕሬዝደንቶች ባሉበት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

አገልግሎቶቹ አንድ ተገልጋይ ባለበት ሆኖ የዳኝነት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል እና የተገልጋዮችን ጊዜ ፣ጉልበትና ወጪ የሚያስቀር ሲሆን ፍርድ ቤቱ አሰራሩን ወደ ዲጅታል የማሸጋገር ጥረት አካል በማድረግ በቀጣይ የዲጅታል ቪድዮ ኮንፍረንስ እና የፍርድ ቤት ክስ ጉዳይና የኦንላይን ደንበኞች ቀጠሮ ማሳወቂያ አገልግሎቶችን ወደ ክልሉ ዞኖች ለማስፋፋት እቅድ ተይዞ እንደሚሰራ ተገልጿል።

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እንግዶቹን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በሶማሊ ክልል የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝትም ተካሂዷል።

Previous Article የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉብኝት ተካሄደ
Next Article በአስማሚነት ክህሎት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረዉ የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
Print
731