የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተደረገ
/ Categories: News

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የፌደራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በቀን 22/09/2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ረቂቅ መመሪያው ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና የሚመለከታቸው የፍርድ ቤት ሰራተኞች እንዲሁም የፍርድ ቤት ተገልጋዮች ሰነዶችን በዲጂታል መንገድ ማቅረብና መከታተል እንዲችሉ እና ከመዝገብ አያያዝ ጋር ያሉ የአሰራር ክፍተቶችን ለማስተካከል የሚረዳ መሆኑን አውስተው ባለጉዳዮች በአካል ፍርድ ቤት መምጣት ሳይጠበቅባቸው በተዘረጋው የኤሌክትሮኒክ ስርአቶች በመጠቀም ባሉበት ሆነው በማንኛውም ግዜ የክርክር ሂደታቸውን እንዲያከናውኑ የሚረዳ አሰራር ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ይህ ረቂቅ መመሪያ አሰራሩ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖረውና ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል በመድረኩ ከዳኞች የሚነሱ ግብዓቶች ረቂቅ መመሪያውን ከማጠናከር ባለፈ ዳኞች እየመጣ ካለው አዲስ ስርአት ጋር እንዲላመዱ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡

የረቂቅ መመሪያውን ገለጻ ያቀረቡት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሃላፊ እና የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት የኮሚቴ አባል ዳኛ አበበ ሰለሞን ሲሆኑ ገለጻውን ተከትሎ ሰፊ ውይይት በማድረግ በዝግጅት ኮሚቴው አወያይነት በርካታ ግብዓቶችን ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

ረቂቅ መመሪያው ላይ ከዚህ ቀደም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ የግብዓት ማሰባሰብ መከናወኑ የሚታወስ ነው።

Previous Article ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሴት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ
Next Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከኡጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት (ቺፍ ጀስቲስ) ክቡር ሚ/ር አልፎንሴ ኦዊኒ ዶሎ ጋር ተወያዩ፡፡
Print
922