የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሔደ
/ Categories: News

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሔደ

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ውይይት ተካሔደ፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች በተገኙበት የተካሔደው የዚህ መድረክ ዓላማ በፍርድ ቤቶቹ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ለመገምገም እና ለመወያየት ሲሆን በመድረኩም ላይ የየፍርድ ቤቶቹ የተጠቃለለ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ፍርድ ቤቶቹ ግልጽ ችሎቶችን ለማጠናከር፣ የዳኝነት ተጠያቂነት ሥርዓትን ለማስፈን፣ በግልጽ ችሎት የመዳኘት መብትን ለማረጋገጥ፣ የተገልጋይ እርካታ ለማሳደግ፣ የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍና ለማሳደግ፣ የዳኝነት ጥራት ለማጎልበት የተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁም የመዛግብት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል፡፡

የየፍርድ ቤቶች የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ከቀረበ በኋላ በዕቅዶቹ ይዘት እና አቀራረብ ላይ በመድረኩ ተሳታፊዎች የተነሱ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ግብአት በመሆን የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የ2018 ዓ.ም የተጠቃለለ ዕቅድ ለማዳበር እንደሚያስችልም በመድረኩ ላይ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ በ2017 ዓ.ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት መልካም አፈጻጸም የታየበት መሆኑን አንስተው ለተገኘው አበረታች ውጤትም የፍርድ ቤቶቹን አመራሮች እና ክቡራን ዳኞችን በማመስገን በ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ በትኩረት ለተሻለ አፈጻጸም መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

Previous Article የፕላዝማ ችሎት እና ኢ- ፋይሊንግ አገልግሎት በጋንቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ ተጀመረ
Next Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎች ልዩ ዕትም ቁጥር 01 ለህትመት በቅቷል
Print
436