የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሰጠው አንድም የዳኝነት ሹመት የለም
/ Categories: News

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሰጠው አንድም የዳኝነት ሹመት የለም

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ለመተግበር ያስችለው ዘንድ የተከማቹ መዛግብትን በቅድሚያ ማጥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ጊዜያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ያቀረበውን ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጉባዔው በፌዴራል ዳኝት አስተዳደር አዋጅ  ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 26 (2) ከአንድ ፍርድ ቤት ወደ ሌላ የፍርድ ቤት ደረጃ በጊዜያዊነት ዳኞችን መድቦ የማሰራት ስልጣኑን ተጠቅሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሸክምን ይወጣሉ ያላቸውን አራት የከፍተኛ ፍርድ  ቤት ዳኞች ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የመዝገብ ክምችት እንዲያጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡  ይህንኑ ውሳኔም መሰረት በማድረግ የተመረጡና ዳኞቹ በተመደቡበት ስራ ላይ ተገኝተው ውዝፍ መዛግብትን እየመረመሩ እና እያጠሩ ይገኛሉ፡፡

ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “ዳኞችን ከህግ አግባብ  ውጪ እየሾመ ነው” በሚል ተገቢነት የሌለው መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ተገንዝቧል፡፡  ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከላይ በተጠቀሰው እውነታ መሰረት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ተገቢነት የሌለው መሆኑን በአጽንኦት እየገለጸ የዚህ የተሳሳተ መረጃ ምንጭ የሆኑ አካላት ቢያንስ ተቋማቱ ስልጣንና ኃላፊነት ያገኙባቸውን አዋጆች አንብበውና ተረድተው ሃሳቦቻቸውን እንዲገልጹ እና ጥያቄዎቻቸውን እንዲያቀርቡ እንመክራለን፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Previous Article በሃገራችን የሰብዓዊ መብትን ለመጠበቅም ሆነ ለማስከበር በቂ የህግ ማዕቀፍ ያለ መሆኑ ተገለጸ
Next Article «ትልቁ የመሪዎች መለያ አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ለመማር ዝግጁ መሆን ነው»
Print
139