የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንጻ ግንባታ ያለበት ደረጃ ተገመገመ
/ Categories: News

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንጻ ግንባታ ያለበት ደረጃ ተገመገመ

አዲስ እየተገነባ ያለው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንጻ ያለበት ደረጃ በዛሬው እለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በተገኙበት በቀን 23/12/2017 ዓ.ም ተገምግሟል፡፡

ግንባታው መልካም አፈጻጻም ላይ የሚገኝ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን በዚህም መሰረት በግንባታ ላይ የሚገኙት ሕንጻዎች በሶስት ብሎኮች ተከፍለው እያንዳንዱ ብሎክ በቅደም ተከተል እየተጠናቀቀ ለአገልግሎት ዝግጁ የሚሆንበት ሂደት ላይ በመወያየት የመጀመሪያው ብሎክ በቀጣይ አዲስ ዓመት ዝግጁ የሚሆንበት እና ለፍትሐብሄር ችሎቶች አገልግሎት በሚሰጥበት ሁኔታ እንዲሰራ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተተገበሩ የሚገኙ የፍርድ ቤት ዲጂታላይዜሽን ስራዎችን በመጎብኘት በቀጣይ በሚሰራው አዲሱ ሕንጻ ላይም በተሻለ የሚተገበሩበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

Previous Article የተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወጣ
Next Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የአሰራር ስርዓት መመሪያ ላይ የቫሊዴሽን ወርክሾፕ ተካሄደ
Print
399