Friday, July 4, 2025 / Categories: News የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አደረገ በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ የሚስተዋሉ ክፍተቶችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም መፍትሄዎች ማስቀመጥ የሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር የዉይይት መድረክ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ መድረኩ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተዘጋጀ ሲሆን ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት የታዩ ክፍተቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የፍትህ ስርዓቱ ዉጤታማ የሚሆንበትን ሁሉን አቀፍ አሰራር እዉን የማድረግ ዓላማ ያለዉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንዳሉት ከፍርድ ቤቱ ጋር ስራቸዉ ግንኙነት ባላቸዉ ባለድርሻ ከሆኑ አካላት ጋር መወያየት ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት ሊታረሙና ሊሻሻሉ የሚገቡ አሰራሮችን ለመፈተሽ ፣ጉድለቱን ለመሙላት እድል የሚፈጥር ከመሆኑ ማሻገር ለሃገር አለኝታ እና ለህብረተሰቡ ተዓማኒ ተቋም ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል ፡፡ አክለዉም ዘርፈ ብዙ እና ሁሉን አቀፍ አሰራሮችን በማጠናከር በጋራ ለመስራት ለሚፈልጉ ተቋማት በሩ ክፍት እንደሆነ ገልፀዉ እንዲህ አይነት መድረኮች በአይነትና በይዘት በመለያየት በቀጣይነት የሚዘጋጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዉስንነቶችን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ሚና፣የፌዴራል ዳኞች ኢንስፔክሽን አገልግሎት አሰጣጥ ፣የመዛግብት አፈፃፀም እና አገልግሎት አሰጣጡን ተገማች፣ቀልጣፋና ዉጤታማ ከማድረግ አንፃር የታዩ ተግዳሮቶች በዳኛ አጃማ ጋዲሳ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለዉይይቱ የሚሆን መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል የፍርድ ቤት መረጃዎች በዘመናዊ የመረጃ ስርዓት በማስተሳሰር በአነስተኛ ወጭ የሚተገበር ፍትህ ለህብረተሰቡ ለመስጠትና አገልግሎቱን ለማዳረስ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እየተገበሯቸዉ ያሉትን የለዉጥ ስራዎች ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዳኝነት ስራዉን ለማሻሻል ጥቅም ላይ የዋሉ አመርቂ ዉጤት ካስመዘገቡባቸዉ የመረጃ ተግባቦት ቴክኖሎጂ (ICT) ዉጤቶች በዝርዝር ለተሳታፊዎች ያቀረቡት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ወርቁ ፍርድ ቤቶች በቀጣይ እየሰሯቸዉ ያሉ የቴክኖሎጂ ስራዎች በአገልግሎት አሰጣጡን መሰረታዊ ለዉጥ ማምጣት የሚያስችሉ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ከመድረኩ ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ጉዳዩ በሚመለከታቸዉ ዳኞችና የስራ ክፍል ኃላፊዎችን እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸዉ ሲሆን ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነትን እንዲሰፍን ስርዓትን ሊያሻሽል እና ጠንካራ ተቋም መፍጠር የሚያስችሉ ስርዓቶችን ለመገንባት የተሰጡ ሃሳብ አስተያየቶችን ለቀጣይ ስራ በግብዓትነት ይወስዳሉ ተብሏል ፡፡ Previous Article የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዋጅ ማሻሻያ እና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ Next Article የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት አቀረበ Print 712