Thursday, June 12, 2025 / Categories: News የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከኡጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት (ቺፍ ጀስቲስ) ክቡር ሚ/ር አልፎንሴ ኦዊኒ ዶሎ ጋር ተወያዩ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከኡጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት (ቺፍ ጀስቲስ) ክቡር ሚ/ር አልፎንሴ ኦዊኒ ዶሎ ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም አፍሪካ ተኮር የሆኑ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎችን በውጤታማነት ለመተግበር ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ወሳኝ ሚና እና በአህጉር ደረጃ በተቋቋመው የአፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች አማራጭ የሙግት መፍቻ መድረክ (African Chief Justices ADR Forum) ኢትዮጵያ በአባልነት መሳተፍ በምትችልበት ሁኔታ እንዲሁም በሌሎች የዳኝነት ስርዓት ማሻሻያ ስራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡ የአፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች አማራጭ የሙግት መፍቻ መድረክ እ.ኤ.አ በ2024 በዩጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አስተባባሪነት ተመስርቶ ባሳለፍነው ግንቦት ወር አጋማሽ ላይ በዩጋንዳ ካምፓላ የ26 አገራት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የመጀመሪያ ጉባኤውን ማከናወኑ ይታወሳል፡፡ Previous Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተደረገ Next Article የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ልዑካን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ Print 418