Friday, December 5, 2025 / Categories: News የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ ኢኒስቲትዩት 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስናን ቀን አከበሩ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ ኢኒስቲትዩት “ትወልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር ”በሚል መሪቃል 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስናን ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም አክብረዋል፡፡ ዕለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዘዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ፀረ ሙስና በፍርድ ቤቶች እየተተገበረ ያለውን ስትራቴጂያዊ ማሻሻያዎች ጋር የሚዛመድ በመሆኑን ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው ሰራተኞች የአገልጋይነት ስሜት በመላበስና በስነምግባር ታንጸው መገኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ አክለውም ትውልድን በሥነ ምግባር ማነጽ ተቋማዊ ስነ ምግባር ባህልን ለማሳደግ የሚረዳ በመሆኑ ዓለማቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ሲከበር በዳኝነት ስርዓት ውስጥ ፍትህን ማስፈንና ታማኝነትን እንዲሁም የህዝብን አመኔታ ለማሳደግ ያለውን አገራዊ ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው አንዳንድ ሀገሮች በሙስና ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸው ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ መቻላቸውን ገልጸው በተለይ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከሚመራባቸው መርሆች አንዱ ህግን ማስከበር በመሆኑ ከፍርድ ቤቶች ጋር የሚጋራው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች የሃብት ምዝገባ ሰነድ ርክከብ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ አመራሮችን በመወከል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ሰነዱን አስረክበዋል ፡፡ በመድረኩ በተለያየ ጊዜ የተጠኑ ጥናቶችን መሰረት ያደረገ በአገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ የሚታዩ የአሰራር ችግሮችንና የመፍትሄ ሃሳብን ያመላከተ በድምፅ የተቀናበረ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ በቀረበው ሰነድ እና በተሳታፊዎች የተሰጡ ገንቢ ሃሳቦችን በግብዓትነት በመውሰድ ለቀጣይ በሥራ ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዘዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ከብልሹ የጸዳ ትውልድን በመፍጠርና የህግ መሰረት ያለው ወጥ የሆነ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተቋምን በአሰራር በማሻሻል ሙስናን ለመታገል ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ Previous Article የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልወውጥ አደረጉ Next Article ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን በተመለከተ ለተከላካይ ጠበቆች ለሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጠ Print 411