Sunday, July 25, 2021 / Categories: News የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና የአስተዳደር ዘርፍ ክፍል ሃላፊዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የአስተዳደር ዘርፍ ከፍል ሃላፊዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው “ኢትዮጵያን እናልብስ” ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ የሃገራችንን የደን ሽፋን የማሳደግና የአየር ንብረትን የመጠበቅ ኃላፊነታችውን ለመወጣት በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል 600 ሃገር በቀል የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡ በችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ዳኞች ባለፈው ዓመት በዚሁ ቦታ ከተከሏቸው ችግኞች መካከል የጸደቁትን በመኮትኮት የተንከባከቡ ሲሆን ባልጸደቁ ችግኞች ምትክ እና በክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ችግኞችን ተክለዋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ላይ ለተሳተፉ ዳኞች ባስተለለፉት መልዕክት ዳኞች የተከሏቸውን ችግኞች ለመንከባከብና አድገው በአካባቢው ካለው የደን አካል እንዲሆኑ ለማድረግ ፍርድ ቤቱ ሃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት Previous Article የፌዴራል ዳኞች የጉባዔ ተወካዮቻቸውን መረጡ Next Article የዳኞችን ዕውቀት እና ክሕሎት በማጎልበት የዳኝነት አገልግሎት አሠጣጥን ጥራት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው Print 1723