Thursday, March 13, 2025 / Categories: News የፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መልካም ስነ ምግባርን በመላበስ የተቋሙን ራዕይ ማሳካት እንደሚገባ ተገለጸ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መልካም ስነ-ምግባራዊ ባህርይ የተላበሰ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበት ስነልቦና፣ ስነምግባርና አገልግሎት አሰጣጥ በሚል ርዕስ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከተቋሙ ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ለተዉጣጡ 115 ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሊዲያ ደምሴ ስልጠናዉን ሲከፍቱ እንዳሉት ማህበረሰቡ ከፍርድ ቤቱ የሚፈልገዉን የዳኝነት አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት መልካም ሥነ-ምግባርን በመላበስ ከብልሹ አሰራሮች በፀዳ መንገድ አገልግሎት በመስጠት የተቋሙን ራዕይ የማሳከት ዓላማ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ገልፀዉ፤በተጨማሪም አሁን ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተገበራቸዉ ያሉትን የለዉጥ ስራዎች ዉጤታማ ለማድረግ ሁሉም ሰራተኛ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአዉሮፓ ህብርት የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ ፕሮግራም ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አሌክሳንደር አዳም የፍርድ ቤት አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች በሚኖራቸዉ ስነልቦና፣ስብዕና እና ባህሪ እንዲሁም ስነ-ምግባር በፍርድ ቤቱ የሚመጡ ተገልጋዮችን ስብዕና በማይነካና በትልቅ አክብሮት አገልግሎት መስጠት በፍትህ ስርዓቱ ለተቋማዊ ለዉጥ ያለዉን ከፍ ያለ ድርሻ የተለያዩ የዘርፉ ምሁራን የሰጡትን ንድፈ ሃሳብና ማሳያ የጥናት ውጤት በማንሳት እንዲሁም የስነ ምግባር መርሆችን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በምን መልኩ መተግበር እንዳለበት ገለፃ በማድረግ ስልጠናዉን ሰጥተዋል፡፡ በስልጠናዉ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሃሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን በመጨረሻም የስነምግባር ፀረ ሙስናና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሊዲያ ደምሴ በፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም ሰራተኛ የሰነ ምግባር መርሆችን መሰረት በማድረግና በመልካም ስነ ምግባር በታነፀ መልኩ ተገልጋዩን ማህበረሰብ ማስተናገድ እንዳለበት አሳስበዋል። Previous Article የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ ተካሔደ Next Article የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የአንድ መስኮት አገልግሎት እና የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት የመስክ ጉብኝት ተካሄደ Print 1110