የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ ከመተግበር አንጻር ያለዉ እንቅስቃሴን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ
/ Categories: News

የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ ከመተግበር አንጻር ያለዉ እንቅስቃሴን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ

ፌዴራል ፍ/ቤቶችን በራሳቸዉ ኔትወርክ የማስተሳሰር እና አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ መሰረት ይሆን ዘንድ ላለፉት ዓመታት ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እያስገነባ የነበረዉ ክላዉድ የመረጃ ቋት ያለዉ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተጠናቀቀ ይገኛል።

ይህንን ተከትሎ የለሙትን የተለያዩ መተግበሪያዎችን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል እንዲቻል የፍ/ቤቶች ዲጂታላይዜሽን አሰራርን በተመለከተ በሀገራችን ላሉ ፍ/ቤቶች መነሻ የሚሆን እና የመጀመሪያ የሆነዉ የህግ ማዕቀፍ " የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ ቁጥር 25/2017" ጸድቋል፡፡

በፌዴራል ፍ/ቤቶች እስካሁን ያሉ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምዶች የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸዉ እና እንዲጠናከሩ እንዲሁም ዘላቂነታቸዉ እንዲረጋገጥ መመሪያዉ ከመስከረም 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ እንዲተገበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት በቀን 27/12/2017 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊት ምድብ ችሎት በመገኘት እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ እና ዝግጅት በጎበኙበት ወቅት መልካም ጅምሮች እና ዝግጅቶች እንዳሉ ጠቅሰዉ በሁሉም የፌዴራል ፍ/ቤቶች የመመሪያዉ አተገባበር ላይ በየደረጃዉ ባሉ አመራሮች ድጋፍ እና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች ተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላትም በመመሪያዉ ላይ ግንዛቤ ወስደዉ ጊዜያቸዉን፣ ዉጣ ዉረድ እና ወጪዎቻቸዉን የሚቀንሱ የዲጂታላይዜሽን አሰራሮችን እንዲጠቀሙ በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን።

Previous Article በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑክ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ፣የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ምድብ ችሎት ጎበኙ።
Next Article በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉብኝት አደረገ
Print
323