የፕላዝማ ችሎት እና ኢ- ፋይሊንግ አገልግሎት በጋንቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ ተጀመረ
/ Categories: News

የፕላዝማ ችሎት እና ኢ- ፋይሊንግ አገልግሎት በጋንቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ ተጀመረ

የጋንቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የፕላዝማ ችሎት እና ኢ-ፋይሊንግ አገልግሎት በክልሉ መጀመሩን አስመልክቶ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት በቀን 09/12/2017 ዓ.ም ዉይይት አድርገዋል፡፡

በክልሉ ይህን መሰል አገልግሎቱ በፍርድ ቤቱ መጀመሩ ተገልጋዮች ያለምንም ወጪ እና መንገላታት ባሉበት ሆነዉ ጉዳያቸዉን እንዲያስፈፅሙ እና በአጭር ጊዜ ዉስጥ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ተብሏል፡፡

በዉይይቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የጋንቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ጀምስ ዴንግ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ኡቻላ ኡጁሉ በቀጣይ በጋንቤላ ክልል በሚገኙ ሌሌች ፍርድ ቤቶች የኢ-ፋይሊንግ እና የፕላዝማ ችሎት አገልግሎት አሰጣጡን በማጠናከር የማስፋት ስራ ስለሚሰራበት ሁኔታ እንዲሁም ባለሙያዎችን ለማሰልጠን በጋራ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

Previous Article በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ የተመራ ልዑክ ቡድን "የተቀናጀ የጉዳዮች ማኔጅመንት ሲስተም እና የኤሌክትሮኒክ ሪከርድ ማኔጅመንት"(Integrated Case Management System and Electronic Record Management) ላይ ኬንያ በመገኘት የልምድ ልው
Next Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሔደ
Print
473