ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘመነ
/ Categories: News

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘመነ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘምኗል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ ማንኛውንም የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ በሚከፈለው ብር መጠን ሳይገድብ፣ ባለጉዳዮች ወደ ባንክ መሄድ እና ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት የአሰራር ማሻሻያ አድርጓል፡፡  በዚህ የክፍያ አፈጻጸም ማሻሻያ ስርዓት፡-

1ኛ. ባለጉዳዮች የባንክ የገንዘብ መክፈያ ካርድ (ATM) ከያዙ እና በባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው ላይ በቂ ገንዘብ ካለ በፍርድ ቤቱ ገንዘብ መሰብሰቢያ ክፍል በሚገኝ ``POS`` ማሽን በመጠቀም የአገልግሎት ክፍያቸውን መፈጸም ይችላሉ፡፡

2ኛ. ባለጉዳዮች በሞባይል ስልክ መተግበሪያ (Mobile Banking) ወይም በማንኛውም ሌላ ዘዴ ተጠቅመው ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000280500376 የሚፈለግባቸውን የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ገቢ ማድረግ እንደሚችሉ እና ስለመክፈላቸው በፍርድ ቤቱ የሂሳብ ክፍል (ገንዘብ ቤት) ማረጋገጥ የሚችሉበት እንደሆነም አሳውቋል፡፡

ጠቅላይ ፍድር ቤቱ ባለጉዳዮች ከላይ ተገለጹትን ዘመናዊ የአከፋፈል ስልቶች ተጠቅመው የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያበረታታ እና ቅድሚያ የሚሰጠው እንደሆነ ገልጾ፤ አሰራሩ ያልተመቻቸው ባለጉዳዮች በቀድሞው አሰራር ከ1,000.00 ብር በታች ከሆነ ብቻ በፍርድ ቤቱ ገንዘብ ቤት በመቅረብ በጥሬ ገንዘብ የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚችሉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል የእርስዎንም ሆነ የፍርድ ቤቱን ጊዜ ይቆጥቡ!!

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Previous Article የ2014 አዲስ ዓመት ጅማሬን አስመልክቶ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት ለፌደራል ፍ/ቤቶች ዳኞች የተላለፈ የምስጋና መግለጫ
Next Article የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ
Print
163