Monday, September 9, 2024 / Categories: News ፍርድ ቤቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የፕሮጀክት ስራ ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በቀን 01/13/16 ኣ.ም ከኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የፕሮጀክት ስራ ማስጀመሪያ ውይይት አድርጓል፡፡ በመድረኩ አጠቃላይ የፕሮጀክት መነሻ ስራዎች የደረሱበት ደረጃ እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫ ላይ ገለጻና ውይይት የተደረገ ሲሆን የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ባለሞያዎችም የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፕሮጀክቱ እንደ ሀገር ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚያስችልና የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ታግዞ ፈጣንና ተደራሽ በማድረግ የዜጎችን እንግልት የሚቀንስ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት በኃላፊነት ስሜት ሊሰራና በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ወደ ስራ መገባት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ክቡር ፕሬዚዳንቱ አክለዉም ፕሮጀክቱ ተቋሙን በቴክኖሎጂ ማዘመን ግልፅ እና ጥራት እንዲሁም ቀልጣፋ የሆነ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ነው ብለዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዓርያስላሴ በበኩላቸው ስራው በተቀመጠለት የግዜ ገደብ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር የተለያዩ ባለሞያዎችን በመመደብና በሂደት አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን ከግምት በማስገባት የፍርድ ቤቱን ማህበረሰብ በጋራ የኃላፊነት ስሜት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ተቋማቱ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ጋር በተገናኘ ዘላቂነት ያለው ትብብርና ስኬታማ የአሰራር ዘዴዎችን እንዲፈጥሩ ለማስቻል እና የፍርድ ቤትን አሰራር ይበልጥ ለማዘመን የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ/ም የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡ Previous Article የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ፡፡ Next Article የሲዳማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሄደ Print 226