ፍርድ ቤቱ የስድስት ዓይነት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገለት
Temesgen Alemayehu
/ Categories: News

ፍርድ ቤቱ የስድስት ዓይነት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገለት

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የፍትሕ ፕሮጀክት (USAID’s Feteh (Justice) Activity in Ethiopia አማካኝነት የ1,260 መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገለት፡፡

በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የሶስቱም ፌደራል ፍ/ቤቶች ፕሬዚደንቶች እና ም/ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም የስድስት ዓይነት የመጽሐፍት ርክክብ የተደረገው በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የፍትሕ ፕሮጀክት ኃላፊ (Feteh Project Chief of Party) በሆኑት በሚስተር ዴቪድ ዴ ክሊስ እና በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት መካከል ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በድጋፍ የተለገሱለት አራቱ መጽሐፍት በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት፣ በወንጀል ሕግ፣ በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ፣ እና በታክስ ሕግ (Ethiopian Constitutional Law, Ethiopian Criminal Law, Ethiopian Employment Law and Ethiopian Tax Law) ላይ የተዘጋጁ ሲሆን ከእያንዳንዳቸው 15 መጽሐፍት በድምሩ 60 መጽሐፍት ለተቋሙ ተበርክተውለታል፡፡

በተመሳሳይም የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ቁጥር 3/2014 እና የፍትሐብሔር ጉዳዮች የክርክር ሒደት ሥርዓተ-ችሎት ሕትመት ድጋፍ በማድረግ ከእያንዳንዳቸው 600 ቅጅ በድምሩ 1,200 ቡክሌቶችን ለፍርድ ቤቱ አስረክቧል፡፡

በመጽሐፍት ርክክቡ ሥነሥርዓት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት ባደረጉት ንግግር የፍትሕ ፕሮጀክት የስራ ኃላፊዎች በመጽሐፍቱ ሕትመት ላይ ለነበራቸው ሚና እና የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Previous Article በፍርድ ቤቶች መልስ ሰጪን ሳያስቀርቡ ይግባኝን መዝጋት ወይም «አያስቀርብም» በማለት የሚዘጉ መዝገቦችን በተመለከተ የተካሔደ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት
Next Article የወንጀል ህጉ ለህጻናት ትኩረት አለመስጠቱ ከህጻናት ጋር ተያያዥነት ላላቸዉ ወንጀሎች መበራከት መንስኤ መሆኑ ተገለጸ
Print
6669

Gallery