ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ ስልጠና ለዳኞች እና ለፖሊስ አባላት ተሰጠ
/ Categories: News, CJPO NEWS

ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ ስልጠና ለዳኞች እና ለፖሊስ አባላት ተሰጠ

ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ ስልጠና ለዳኞች እና ለፖሊስ አባላት ተሰጠ

ጳጉሜን 03/2018 ዓ/ም (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት፤ ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ሂደት ትግበራን በተመለከተ ለመርማሪ ፖሊስ አባላት እና ለክቡራን ዳኞች በሁለት ዙር የተከፈለ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

‎ይህ ስልጠናው በህጻናት ዙሪያ የሚሰሩ የፍትህ አካላትን ሙያዊ አቅም እና የስነ-ልቦና ዝግጁነት ለማጎልበት ያለመ ስልጠና ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙር ህጻናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የምርመራ ስራን ለሚያከናውኑ የፖሊስ አባላት እና አመራሮች ህጻናትን ያማከለ የምርመራ ሂደት አተገባበርን ለማጠናከር የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

‎እንዲሁም በሁለተኛው ዙር የስልጣና መርሃ ግብር ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተወጣጡ ዳኞች ህጻናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የዳኝነት አገልግሎት ሲሰጡ የሚገጥማቸውን የስነ-ልቦና ጫና ተቋቁመው ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በተለይም የስሜት ብስለትን የማዳበር ክህሎት እና ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍርድ ሂደት ትግበራ ላይ ያተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮች ተዳስሰዋል።‎

‎በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክብርት ዳኛ ህውስት አሸናፊ በስልጠናው ላይ እንደገለጹት፤ በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓት በመገንባት ረገድ የላቀ ፋይዳ እንዳለው በማንሳት፣ ስልጠናው የህጻናትን የላቀ ጥቅም በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የፍትህ አካላት ያላቸውን ሰፊ ሚና በተግባር እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

Previous Article BRICS Chief Justices' Forum Concludes
Next Article የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተገለጸ
Print
436