ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አስተባበሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ
/ Categories: News

ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አስተባበሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል።

‎‎ዳይሬክቶሬቱ ለህጻናት ተስማሚ፣ ምቹ፣ ተደራሽና መብት ተኮር የፍትህ ስርዓት የመገንባት ዓላማዉን እውን ለማድረግ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸዉን ዋና ዋና ስራዎች፣ በጥንካሬና በውስንነት የተለዩ ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ የተያዙ የትኩረት አቅጣጫዎች በዘርፉ ባለሙያዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

‎የማዕከላቱን ተደራሽነት በማሳደግና ወጥ አሰራር እንዲከተሉ በማስቻል ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ባለድርሻ አካላት የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚሰጡትን አገልግሎት በሚመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራባቸው በመድረኩ የተነገረ ሲሆን የማስማማት ተግባርን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

Previous Article በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ለተቋሙ የቀድሞ አመራሮች ገለጻ ተደረገ
Next Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን መፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
Print
499