ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
/ Categories: News

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ‎

‎ግንቦት 18/2018 ዓ/ም (ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

‎የህጻናት ፍትህ አስተዳደርን ለማዘመን እንደሚያግዝ የተገለጸው ይህ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በተገኙበት ተከናውኗል።

‎ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በዳኝነት አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ በትኩረት የሚሰራበት መሆኑ እና ለህጻናት ምቹ ችሎትን ከመፍጠር አንጻር የሚሰሩ ስራዎች የዚሁ ግብ አካል መሆናቸው በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

Previous Article ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ ላይ የቫሊዴሽን ወርክ ሾፕ ተካሄደ
Next Article በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ለተቋሙ የቀድሞ አመራሮች ገለጻ ተደረገ
Print
407