‎የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ
/ Categories: News

‎የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ

የሸሪዓ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሂዷል።

‎‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ዘንድ በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ ችግሮች በጥናት እንዲለዩ መደረጉን ጠቅሰው፤ አብዛኛው ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት የማቋቋሚያ አዋጁ ሲሻሻል መሆኑን ጥናቱ ማመላከቱን ገልጸዋል።

‎በጥናቱ መነሻነት በአዋጁ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ሊያርም የሚችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለተከበረዉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩንም አስታውሰዋል።

‎ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ የውይይት መድረኩ ረቂቅ አዋጁ ችግሮችን በምን አይነት መልኩ መፍታት ይችላል የሚለውን ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለማስገንዘብ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎‎የአጥኚ ቡድን እና የአርቃቂ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ዳኛ መሐመድ አህመድ የረቂቅ አዋጅ ዝግጅት ሂደት እና የነበሩ ችግሮችን እንዴት መቅረፍ ይቻላል የሚለውን ሊያሳይ በሚችል መልኩ ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል።

‎‎በቀረበው የረቂቅ አዋጅ ላይ የቋሚ ኮሚቴ አባላት

‎ሀሳብ አስተያቶችን በማንሳት የተወያዩ ሲሆን፤ በጥናት ላይ ተመስርቶ ረቂቅ አዋጁን ማዘጋጀት መቻሉን አድንቀዋል።   

Previous Article የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ምስለ ችሎት ውድድር ተካሄደ
Next Article የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው
Print
182