የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ መካሄድ ጀመረ
/ Categories: News

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ መካሄድ ጀመረ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል።
‎መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዳኛ አበበ ሰለሞን እንደገለጹት፤ መድረኩ በፍርድ ቤቱ የተመዘገቡ ስኬቶችንና መልካም ውጤቶችን በመገምገም የተጀመሩ ዘላቂ የለውጥ ጥረቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መሆኑን ገልጸው፣ ሥራዎች ከቁጥራዊ መግለጫ ባሻገር የሚጨበጥ ውጤት የሚያስገኙ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል።
‎‎ፍርድ ቤቶች እየተገበሩት ባለው የዲጂታላይዜሽን ሂደት አገልግሎት ሰጪው አካል ራሱን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ማዋሃድ እንደሚገባው የጠቆሙት ዳኛ አበበ፣ አጠቃላይ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ መሆን እንደሚገባው ገልጸዋል።
‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስትራቴጂክ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በቀረበው ሪፖርት፤ የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፣ የተመዘገቡ መልካም አፈጻጸሞችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሠረት በማድረግ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
‎ዓመታዊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኞች መድረክ በነገው ዕለትም በሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችና የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚቀጥል ይሆናል።

Previous Article ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት አመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ላይ ተወያዩ
Next Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ በስልጠናና በእውቅና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ
Print
524