Monday, August 31, 2026 / Categories: News የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ በስልጠናና በእውቅና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። በመድረኩ በመሰረታዊ የሠራተኞች መብቶችና ግዴታዎች፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣንና ኃላፊነት እንዲሁም በልዩ ልዩ የሕግ ማዕቀፎችና ድንጋጌዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሮን ደጎል ተሰጥቷል። በቀረበው ስልጠና ላይ ከሰራተኞች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በሥነ-ምግባራቸውና በታታሪነታቸው የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሶስት ሰራተኞች እንዲሁም ተቋሙን ለረዥም ዓመታት አገልግለው በጡረታ ለተሰናበቱ አምስት ሰራተኞች የዕውቅናና የምስጋና መርሃ-ግብር ተካሂዷል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በመድረኩ የማጠቃለያ ንግግራቸው፣ ባለፉት ሁለት ቀናት የተካሄዱት መድረኮች ፍርድ ቤቱ ያከናወናቸውን ተግባራት፣ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንና የተወጣበትን መንገድ በመገምገም የቀጣይ የጋራ አቅጣጫ የተቀመጠበት መሆኑን ገልጸዋል። Previous Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ መካሄድ ጀመረ Next Article BRICS Chief Justices' Forum Concludes Print 227