የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፍርድ ቤቶች አሰራርን እና የሰበር ውሳኔዎች ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት(MOU) በቀን 05/06/2018 ዓ.ም ተፈራርሙ

1154

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡

በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

911

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በዳኝነት ስርአት ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ በቀን 03/06/2018 ዓ.ም ተካሂዷል።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶች የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ተግባራት ላይ ገለጻ ተደረገ

1112

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ ተሿሚ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ክቡር አቶ ልዑል ካህሳይን እና ክቡር አቶ ምትኩ ማዳን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች ጋር በቀን 02/06/2018 ዓ.ም ትውውቅ እና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ተግባራት ላይ ገለጻ እና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ማብራሪያ የቀረበላቸው ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ 2018 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት የውይይት መድረክ ተካሄደ

1675

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 የመጀመሪያዉ መንፈቅ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የውይይት መድረክ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተደርጓል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን እና የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አፀደቀ

1024

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን እና 50 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

First2345791011Last