የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአምስት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የውይይትና ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል

3

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት፣የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥልጠና መመሪያ፣የእግድ አሰጣት እና አተገባበር ላይ፣በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሕ መዘግየት ምክንያቶች እና ማነቆዎች በሚል በተዘጋጀ ሞጁል ላይ እንዲሁም የወሲባዊ ጥቃት ወንጀሎችን በተፋጠነ እና ተጎጅ ተኮር በሆነ መንገድ ለመዳኘት የሚያግዝ ማኑዋል ላይ ለሁለት ቀናት የቆየ የውይይትና ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተዘጋጀ ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ

4

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በጋራ በመሆን በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ባዘጋጁት ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ በቀን 22/03/2017 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገልጋዮች ለፍ/ቤት የሚቀርቡ መዛግብትን ባሉበት አካባቢ ሆነው ማስከፈት የሚችሉበት (e-filing) ሶፍትዌር እና የዳኞች መዝገብ መከታተያ ( judge’s Dashboard) ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ

34

በፍርድ ቤቱ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ ስርአት ተቋሙ እያከናቸው ከሚገኘው መጠነ ሰፊ የዲጅታላይዜሽን ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን የተገልጋዮችን እንግልት እና ወጪ የሚቀንስ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር የሚያሰፍኑ እና ለዳኞች ምቹ የስራ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው::

በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

44

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ከፌደራል ፍትህና ህግ ኢኒስቲትዩት እንዲሁም ከኢትዮጵያ አስማሚነትና ግልግል ዳኝነት ማዕከል(EMAC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ያተኮረ ከቀን 05/03/2017-07/03/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ በሚቋቋም ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል

87

ከፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች፣ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስራ ሃላፊዎች የተሳተፉበት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ በሚቋቋም ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከቀን 29/02/2017 እስከ 30/02/2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ልዑካን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

99

የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር እንዲሁም በኢትዮጵያ የቻይና ምክትል አምባሳደርን ያካተተ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 19/02/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ 

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ

237

በቀን 02/02/17 ዓ.ም በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሶች ማለትም የፍ/ቤት ዲጂታላይዜሽን ስራዎች፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ላይ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፣ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(INSA)፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተቋማት በተገኙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቋል፡፡   

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት በይፋ ተጀምሯል

306

በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 በተደነገገው መሠረት በየዓመቱ ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ድረስ ለሁለት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው እንደቆዩ የሚታወስ ሲሆን መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ከዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሯል።

1345678910Last