የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

815

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ የልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 18/06/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ ፍትህ ሚኒስትር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ

1169

የህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ ፍትህ ሚኒስትር ሚስ ሂ ሮንግ እንዲሁም በኢትዮጵያ የቻይና ሪፐብሊክ አምባሳደር የሆኑት ሚስተር ቺን ሃይ ከልዑክ ቡድኖቻቸው ጋር በመሆን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 6/6/2017 ዓ.ም በመገኘት የጋራ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን የስራ ጉብኝትና ውይይት አድርገዋል፡፡

"ስነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልእኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ለፌደራል ፍርድ ቤቶች መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ

974

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለፌደራል ፍርድ ቤቶች መካከለኛ አመራሮች "ስነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልእኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ከፌደራል ፍርድ ቤቶች፣ ከፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ፅ/ቤት እንዲሁም ከፌደራል ፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና ሬጅስትራሮች የተሳተፉበት የሁለት ቀናት ስልጠና የካቲት 5 እና 6 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት እቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ

1162

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት እቅድ አፈፃጸም ሪፖርት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች፣ ክቡራን ዳኞች እንዲሁም የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር የስራ አመራር ቦርድ አባላት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

979

ኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር የስራ አመራር ቦርድ አባላት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/05/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የቦርድ አባላቱ በቆይታቸው የፌደራል ፍርድ ቤቶችን አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች ላይ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በተለይም ፍርድ ቤቶቹ በቴክኖሎጂ ረገድ እየሰሩባቸው ያሉ የለውጥ ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይት እንዲሁም ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት ዓመታዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ

995

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት ዓመታዊ የውይይት መድረክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት በቀን 20/05/2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

1032

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በቀን 19/05/2017 ዓ.ም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣የከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታ፣ የዳኞች ተወካዮች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽን እና ኤሌክትሮኒክ ሪከርድ አመራር አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ

1070

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በፌደራል ፍርድ ቤቶች የኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽን እና ኤሌክትሮኒክ ሪከርድ አመራር የአፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ ሃላፊዎችና ተጠሪ ዳኞች፣ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከፌደራል ማረሚያ ቤት፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ጠበቆች ማህበር፣ ከህግ ባለሙያዎች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቀን 19/04/2017 ዓ.ም የውይይት መድረክ ተካሂዷል።  

First7891012141516Last