የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር የስራ አመራር ቦርድ አባላት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

64

ኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር የስራ አመራር ቦርድ አባላት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 22/05/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የቦርድ አባላቱ በቆይታቸው የፌደራል ፍርድ ቤቶችን አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች ላይ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በተለይም ፍርድ ቤቶቹ በቴክኖሎጂ ረገድ እየሰሩባቸው ያሉ የለውጥ ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይት እንዲሁም ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት ዓመታዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ

70

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት ዓመታዊ የውይይት መድረክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት በቀን 20/05/2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

88

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ ግንባታ ማስጀመሪያ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በቀን 19/05/2017 ዓ.ም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣የከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታ፣ የዳኞች ተወካዮች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽን እና ኤሌክትሮኒክ ሪከርድ አመራር አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ

150

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በፌደራል ፍርድ ቤቶች የኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽን እና ኤሌክትሮኒክ ሪከርድ አመራር የአፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ ሃላፊዎችና ተጠሪ ዳኞች፣ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከፌደራል ማረሚያ ቤት፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ጠበቆች ማህበር፣ ከህግ ባለሙያዎች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቀን 19/04/2017 ዓ.ም የውይይት መድረክ ተካሂዷል።  

ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከበረ

132

ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ‹‹የሴቷ ጥቃት የኔም ነዉ፣ ዝም አልልም›› በሚል መሪ ቃል የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች፣ ከፍትህ ተቋማት የተገኙ ሃላፊዎች፣ የመንግስት ሆስፒታሎች የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ/ም ተከብሯል፡፡ 

ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከበረ

246

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ፣ በአገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤቱ ዳኞችና የአስተዳደር ሠራተኞች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

245678910Last