ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶች የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ተግባራት ላይ ገለጻ ተደረገ

328

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ ተሿሚ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ክቡር አቶ ልዑል ካህሳይን እና ክቡር አቶ ምትኩ ማዳን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች ጋር በቀን 02/06/2018 ዓ.ም ትውውቅ እና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ተግባራት ላይ ገለጻ እና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ማብራሪያ የቀረበላቸው ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ 2018 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት የውይይት መድረክ ተካሄደ

494

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 የመጀመሪያዉ መንፈቅ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የውይይት መድረክ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተደርጓል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን እና የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አፀደቀ

204

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን እና 50 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመንፈቅ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ

322

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 2018 በጀት ዓመት የመንፈቅ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በቀን 27/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሶስቱም ፍርድ ቤቶች አመራሮችና የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016፣ መመሪያዎች እና ኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ አጻጸም (e-GP) ስርዓት ክህሎት ላይ ስልጠና ተሰጠ

226

ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016፣ መመሪያዎች እና ኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ አጻጸም (e-GP) ስርዓት ክህሎት ላይ ከጥር 21 እስከ 23/2018 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡

ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጂስራርና ችሎት አገልግሎት ክፍል ለተውጣጡ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

121

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሬጂስትራርና ችሎት አገልግሎት ክፍል ለተውጣጡ ሰራተኞች በሙስና ምንነት፣ በሙስና ባህሪያት፣ በአዋጅ 881/2007 የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች፣ የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሥነ ምግባር ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ በቀን 23/5/2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል::

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውይይት እና ጉብኝት አደረጉ

246

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም በመገኘት ወደፊት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በ19ኛው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል ተቋማት የሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአልጀሪያ አልጀርስ ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

453

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት እና የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ በሆኑት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ወዬሳ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ማክሰኞ ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም አልጀርስ ሲደርስ በአልጀሪያ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

245678910Last