የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህጻናት ማቆያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህጻናት ማቆያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ Wednesday, August 9, 2023 2284 የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አዲስ ለሚያሰራው የህጻናት ማቆያ የሚሆን ግምታቸው ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡ Read more
ዜና መግለጫ ዜና መግለጫ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡ Thursday, August 3, 2023 2621 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ እና በሕግ በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተናገድ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሰላም እና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ተግባራትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ በዚህ መሰረት በ2015 በጀት ዓመት በነበረዉ የመዛግብት አፈጻጻም አንጻር ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 213,116 መዛግብት ቀርበዋል። ከእነዚህም ዉስጥ ለ184,467 (86.56%) መዛግብት እልባት መስጠት የተቻለ ሲሆን 28,675 (13.44%) መዛግብት ደግሞ ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2014 በጀት ዓመት ለፌ/ፍ/ቤቶች የቀረቡት 209,317 መዛግብት ሲሆኑ ዕልባት ያገኙት ደግሞ 176,767 ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት መዛግብት በ2014 በጀት ዓመት ከቀረቡት በ3,799 (1.8%) ከፍ ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ ዕልባት ያገኙትም በ7,670 (4.3%) መዛግብት ከፍ ያሉ ናቸው፡፡ የፍርድ ቤቶቹ አፈጻጸም በተናጠል ሲታይ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት 26,185 መዛግብት ቀርበው ለ19,201 ዕልባት የተሰጠ ሲሆን 6,984 መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በ2015 በጀት ዓመት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የመዛግብት ብዛት 33,721 ሲሆን 26,301 መዛግብት ዕልባት አግኝተዋል፡፡ ወደ 2016 የተሻገሩት መዛግብት ብዛትም 7,420 ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት 153,210 መዛግብት ሲሆኑ 138,965 ዕልባት በማግኘታቸው 14,245 ወደ 2016 በጀት ዓመት ተላልፈዋል፡፡ Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር ተከናወነ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር ተከናወነ Tuesday, July 25, 2023 2478 (ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም፣) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክቡራን ፕሬዚዳንቶች ፣ ክቡራን ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ተከናወነ፡፡ Read more
በቤተሰብ አስማሚነት ላይ የተዘጋጀ የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሔደ በቤተሰብ አስማሚነት ላይ የተዘጋጀ የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሔደ Friday, June 30, 2023 2107 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በፍርድ ቤት መር አስማሚነት በተለይም በቤተሰብ አስማሚነት (Family mediation) ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች እና ለሶሻል ወርክ ባለሙያዎች ያዘጋጀው የሥልጠና እና የውይይት መድረክ በኢንተር ኮንቲኔታል ሌግዢሪ ሆቴል ተካሄዷል፡፡ Read more
ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር ክህሎት (Leadership) ላይ ሥልጠና ተሰጠ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር ክህሎት (Leadership) ላይ ሥልጠና ተሰጠ Thursday, June 29, 2023 2318 ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር ክህሎት (Leadership) ላይ የተዘጋጀ ሥልጠና በአሜሪካ አገር ከሚገኘውና ችክፍሌ (Chick-fil-A) ከተሰኘው ድርጅት በመጡ ስድስት ባለሙያዎች ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተሰጠ፡፡ ሥልጠናው የመሪነት ጽንሰ-ሐሳብ እና የጥሩ መሪ ስብዕናዎች የተዳሰሱበት ሲሆን በኃላፊነት ላይ የተቀመጡና በሥራቸው ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ሁሉ መሪ (Leader) ሊሆኑ እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡ Read more
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት ተካሔደ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት ተካሔደ Monday, June 26, 2023 2396 በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ላይ በጥብቅና ሙያ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ ጠበቆች በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ገለጻ ተደርጓል፡፡ Read more
ለፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የተገነባው አዲስ ሕንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ለፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የተገነባው አዲስ ሕንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ Tuesday, June 20, 2023 2341 ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ አዲስ የተገነባው ባለሶስት ወለል (G+2) ሕንጻ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ Read more
ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም በዘረመል ምርመራ አጠቃቀም ላይ የተዘጋጀ የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሔደ ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም በዘረመል ምርመራ አጠቃቀም ላይ የተዘጋጀ የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሔደ Monday, June 19, 2023 2863 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም በዘረመል ምርመራ አጠቃቀም ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች ያዘጋጀው የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ከሰኔ 10-11 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሒዷል፡፡ Read more