«ትልቁ የመሪዎች መለያ አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ለመማር ዝግጁ መሆን ነው» «ትልቁ የመሪዎች መለያ አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ለመማር ዝግጁ መሆን ነው» የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ Saturday, July 9, 2022 1749 ክብርት ፕሬዚደንትዋ ይህን የገለጹት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንትና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ የሆኑት ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ «የአመራር ክህሎት» በሚል ርዕስ ያሳተሙትን መጽሐፍ ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ለማስመረቅና ለማስገምገም በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሰጠው አንድም የዳኝነት ሹመት የለም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሰጠው አንድም የዳኝነት ሹመት የለም Tuesday, June 28, 2022 1872 የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ለመተግበር ያስችለው ዘንድ የተከማቹ መዛግብትን በቅድሚያ ማጥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ጊዜያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ያቀረበውን ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ይህንን ተከትሎ ጉባዔው በፌዴራል ዳኝት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 26 (2) ከአንድ ፍርድ ቤት ወደ ሌላ የፍርድ ቤት ደረጃ በጊዜያዊነት ዳኞችን መድቦ የማሰራት ስልጣኑን ተጠቅሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሸክምን ይወጣሉ ያላቸውን አራት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የመዝገብ ክምችት እንዲያጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ Read more
በሃገራችን የሰብዓዊ መብትን ለመጠበቅም ሆነ ለማስከበር በቂ የህግ ማዕቀፍ ያለ መሆኑ ተገለጸ በሃገራችን የሰብዓዊ መብትን ለመጠበቅም ሆነ ለማስከበር በቂ የህግ ማዕቀፍ ያለ መሆኑ ተገለጸ Monday, June 13, 2022 1974 “ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች አተገባበር በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች” በሚል ርዕስ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የህግ ባለሙያዎች የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናው ዋና ዓላማ የህዝብ ጥቅም የሚነኩ ክርክሮች ጽንሰ ሃሳባዊ ማዕቀፎችን፣ በኢትዮጵያ ሃገራዊ የዳኝነት ስልጣን ወሰን የሰብዓዊ መብቶችን የተመለከቱ ክርክሮችን ለመዳኘት የሚያግዙ በስራ ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም መሰረታዊ መብቶችንና ነጻነቶችን ለመተግበር የሚረዱ የህግ ማዕቀፎችን በስልጠናው ለተሳተፉ ዳኞችና ህግ ባለሙያዎች ማስገንዘብ እና የጋራ መረዳት መፍጠር ነው፡፡ Read more
የፍርድ ቤቱን የአስተዳር ሰራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት የሚያጎለብቱ ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ የፍርድ ቤቱን የአስተዳር ሰራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት የሚያጎለብቱ ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ Saturday, June 11, 2022 1555 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ የፍርድ ቤት የአስተዳር ሰራተኞችን አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን የመስጠት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ይህን የገለጹት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ዘርፍ የጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በተዘጋጀ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ በሰጡት የስራ መመሪያ ነው፡፡ Read more
በአስተዳደር ዘርፍ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሰራተኞውን የመፈጸም ዓቅም ለማጎልበት የሰራ መሆኑ ተገለጸ በአስተዳደር ዘርፍ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሰራተኞውን የመፈጸም ዓቅም ለማጎልበት የሰራ መሆኑ ተገለጸ Monday, May 30, 2022 1801 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአስተዳደር ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና 630 ለሚጠጉ የፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ከግንቦት 04 ቀን 2014 እስከ ግንቦት 21 ቀን 2014 ዓ/ም ቢሾፍቱ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት በአራት ዙር ሰጥቷል፡፡ Read more
ሰበር ሰሚ ችሎቱ ሕጋዊነቱ ባልተረጋገጠ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት ኮሎኔል ገሙቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ ሕጋዊነቱ ባልተረጋገጠ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት ኮሎኔል ገሙቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ Tuesday, May 24, 2022 1829 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከቀረበባቸው ክስ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ ህጋዊነቱ ባልተረጋገጠ ሁኔታ የተያዙና ይህ ውሳኔ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በእስር ላይ የሚገኙትን ኮሎኔል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ ለፌዴራል ፖሊስም ተጠርጣሪውን በዛሬዋ ዕለት እንዲለቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተቀናጀ የጉዳዮች አስተዳደር መረጃ ስርዓት (ICMIS) እና ኤሌክትሮኒክ-ሰነድ አስተዳደር ስርዓት (e-RMS) ልማትና ትግበራ ጽንሰ-ተልዕኮ (Inception Mission) መርሃ ግብር ተካሄደ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተቀናጀ የጉዳዮች አስተዳደር መረጃ ስርዓት (ICMIS) እና ኤሌክትሮኒክ-ሰነድ አስተዳደር ስርዓት (e-RMS) ልማትና ትግበራ ጽንሰ-ተልዕኮ (Inception Mission) መርሃ ግብር ተካሄደ Friday, May 13, 2022 1743 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጠውን የዳኝነት አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ራስ-ተግባሪ (Automation) ስርዓት የተደገፈ ለማድረግ የወጠነው ፐሮጀክት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት- ፍትህ ተግባራት ኢትዮጵያ (USAID- Justice Activities-Ethiopia) ድጋፍ ስርዓቱን ለማልማት በአለም ዓቀፍ ጨረታ ያሸነፈው ሲነርጂ ኢንተርናሽና ሲስተምስ የተባለ ድርጅት ጽንሰ-ተልዕኮ መርሃ ግብር (Inception Mission Schedule ) ከግንቦት 1 -5 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ Read more
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሙስና ተግባራት መከላከያና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሙስና ተግባራት መከላከያና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ Thursday, May 12, 2022 1734 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያዘጋጀውን እና በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውይይት ተደርጎበትና ቅቡልነት አግኝቶ ለትግበራ ዝግጁ የሆነውን “በዳኝነት አካል ውስጥ የሚታዩ የሙስና ተግባራት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ” የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች፣ ሰብሳቢ ዳኞች፣ የዳኞች ተወካዮች እና የአስተዳደር ዘርፍ ልዩ ልዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ይፋ አድርጓል፡፡ ስትራቴጂው ይፋ የተደረገበት የውይይት መድረክ ለስትራቴጂው አተገባበር የሚገጁ ሃሳቦችን በማንሸራሸር ይሁንታ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው፡፡ Read more