በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ Monday, January 17, 2022 1389 በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ በተለያየ የሃራችን ክፍሎች የተፈጠሩ ግጭቶች ጋር በተገናኘ በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት አግኝተዋል፡፡ በእያንዳንዱ ፋይል የተከሳሾች ቁጥር በአማካይ ከ 50 – 200 እንደሚድረስ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ ጉዳዩቹ ደግሞ እጅግ ውስብስብ ናቸው ብለዋል፡፡ ክብርት ፕሬዚደንትዋ «ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትሕ፤ ግጭቶች ሲከሰቱ ወይም ከግጭት በኋላ » በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም በተዘጋጀ ሲምፖዚየም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በሀገራችን በተከሰቱ ግጭቶች ሕግንና ሞራልን የጣሱ በርካታ ተግባሮች እንደተከናወኑ ገልጸው በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የተፈጸመው ወንጀል ደግሞ ሊታለፉ ከማይገባቸው ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ Read more
ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ የተሰጠ የፕሬስ መግለጫ ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ የተሰጠ የፕሬስ መግለጫ Tuesday, January 11, 2022 1734 ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍ/ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍ/ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍ/ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍ/ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ” ጉባዔ እንደሚገልጸው በተለያየ ደረጃ የፍ/ቤቱ አገልግሎትም ሆነ ተደራሽነት እያደገ የመጣ ለመሆኑ ፍ/ቤቱ በገለልተኛ የጥናት ተቋም የሰራው የሕዝብ አስተያየት ሰርቬይ “public perception survey” አመልክቷል፡፡ Read more
ዳኞች የዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸምን በሚመለከቱ ሕጎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በየጊዜው ሊያዳብሩ እንደሚገባ ተጠቆመ ዳኞች የዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸምን በሚመለከቱ ሕጎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በየጊዜው ሊያዳብሩ እንደሚገባ ተጠቆመ Sunday, December 26, 2021 1505 ዳኞች ከአገር ኢንቨስትመንት፣ ከሕዝብ ጥቅም እንዲሁም ከግለሰብ ክርክሮች ጋር በተያያዘ በዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸም ዙሪያ የሚወስኑትን ጉዳይ ማየትና መፈተሽ እንዲሁም በሕጎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በየጊዜው ሊያዳብሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ ይህ የተገለጸው ከሶስቱ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች ከዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ Read more
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት መመሪያ አወጣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት መመሪያ አወጣ Wednesday, December 22, 2021 3062 የፍርድ ቤት መር አስማሚነትን የሚያግዝ የአስማሚዎችን የዲሲፕሊን ጉዳዮች የሚመረምር ኮሚቴ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 45(7) መሰረት መቋቋም ስለሚያስፈልገው እና የኮሚቴውንም ዝርዝር ሃላፊነት፤ አወቃቀር እና የተጠያቂነት ወሰን መደንገግ ስለሚያስፈልግ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 45(8) እና 48(4) በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፍርድ ቤት መር የአስማሚነት መመሪያ ወጥቷል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያወጣው መመሪያ የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት መመሪያ ቁጥር 12/2014 በሚል ስያሜ ይጠራል፡፡ Read more
ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት መገኘቱ ተገለጸ ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት መገኘቱ ተገለጸ Sunday, December 19, 2021 1622 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እየተከናወኑ ባሉ የማሻሻያ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘታቸውን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና የአስተዳደር ዘርፍ ሃላፊዎች እንዲሁም የስር ፍርድ ቤቶች ፕዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች በተገኙበት በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ገለጹ፡፡ የውይይት መድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል- ፐሪዝን ፌሎው ሺፕ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሂደት የፍርድ ቤቶች ሚናን አስመልክቶ ዳኞች በሙያቸው ያገኙትን ዕውቀትና እና አመለካከት እርስ በእርስ እንዲለዋወጡ ማስቻል እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማሻሻያ ስራዎች ያስገኙትን ውጤት መገምገም ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ Read more
ፍርድ ቤቱ በስትራቴጂያዊ እና ዓመታዊ ዕቅዱ ላይ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ማብራሪያ ሰጠ ፍርድ ቤቱ በስትራቴጂያዊ እና ዓመታዊ ዕቅዱ ላይ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ማብራሪያ ሰጠ Saturday, December 18, 2021 1647 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና የዲሞክራሲ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ ባዘጋጀው ሶስተኛው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጠ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፍርድ ቤቱ በኩል ዕቅዶቹን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ ከመቅረቡ በፊት በሰጡት አጭር ገለጻ የዳኝነት ዘርፉ በአማካሪ ድርጅት በመታገዝ ስትራቴጂያዊ ዕቅዱን ማዘጋጀቱን፤ የዕቅዱን ይዘትና አዘገጃጀት ሂደት የሚከታተል በየደረጃ ያሉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አባል የሆኑባቸው ዓቢይና ቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋማቸውን፤ በረቂቅ ዕቅዱ ላይ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት መወያየታቸውን እና የተገኙ ተጨማሪ ግብዓቶችን በማካተት ተዘጋጅቶ የጸደቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ Read more
የሙስና ወንጀልን በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ የሙስና ወንጀልን በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ Sunday, December 12, 2021 1534 የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጃ ታደሰ የሙስና ወንጀልን በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል እንደሚገባ ገለጹ፡፡ አቶ ቦጃ ታደሰ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል አከባበርን አስመልክቶ በተዘጋጀ የገንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሙስና ሕዝብ በመንግሥት እና በሕግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣ የማድረግ ጉልበት ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በእጅጉ በማዳከምና በመጉዳት የሞራልና የሥነምግባር ቀውስ እንዲፈጠር የሚያደርገውን የሙስና ወንጀል በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ Read more
ፍርድ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሴቶችና ሕጻናት ሥርዓተ-ችሎት እንዲዘጋጅ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቆመ ፍርድ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሴቶችና ሕጻናት ሥርዓተ-ችሎት እንዲዘጋጅ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቆመ Saturday, December 11, 2021 1164 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሴቶችና ሕጻናት ዙሪያ የሚኖርን የፍትሕ ተገማችነትን ለማስፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሥርዓተ-ችሎት እንዲዘጋጅ እያደረገ እንደሚገኝ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ አስታወቁ፡፡ ም/ፕሬዚደንቱ ይህን ያስታወቁት የፌደራል ፍ/ቤቶች ዓለም ዓቀፍ ፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀንን ሕዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አዳራሽ በፓናል ውይይት ሲከበር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡ Read more