በፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ ለዳኝነት ዘርፉ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ በፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ ለዳኝነት ዘርፉ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ Sunday, August 22, 2021 1977 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኝነት ዘርፉ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በፍትሐብሔርጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ነሐሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ በሥልጠናው የተሳተፉት ብዛታቸው 65 የሆኑ የፍርድ ቤቱ ረዳት ዳኞች፣ ሴክሬታሪዎች፣ የችሎት ፀሐፊዎች፣ ሬጅስትራሮች እና ዳታ ኢንኮደሮች ናቸው፡፡ Read more
የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ዓለም አቀፋዊ የዳኝነት መርሆዎችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ዓለም አቀፋዊ የዳኝነት መርሆዎችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ Sunday, August 22, 2021 2327 የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ዓለም አቀፋዊ የዳኝነት መርሆዎችን እንዲሁም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥትን እና ሌሎች የአገሪቱን ሕጎች መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ረቂቅ ደንቡ ሲዘጋጅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዓለም አቀፍ የሕግ አማካሪ የሆኑት አሜሪካዊው ሚስተር ማይክል ከኒፍ ገለጹ፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሪፎርም አካል በሆነውና ማሻሻያ ተደርጎበት በቅርቡ በዳኝነት አስተዳደር ጉባኤ በጸደቀው የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ከነሐሴ 15-25 ቀን 2013 ዓ.ም በአምስት ዙሮች በመሰጠት ላይ ነው፡፡ Read more
በፍርድ ቤቱ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው በፍርድ ቤቱ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው Sunday, August 15, 2021 1797 በቅርቡ የፀደቀውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ በ2014 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊው ቅድመ-ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 008/2013ን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ለማስተዋወቅና ትግበራውን ለማስጀመር ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል ውይይት ተካሒዷል፡፡ Read more
በፍ/ቤቶች የዳኝነት ነጻነትን፣ ገለልተኝነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገለጸ በፍ/ቤቶች የዳኝነት ነጻነትን፣ ገለልተኝነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገለጸ Saturday, August 14, 2021 1557 በፌደራል ፍርድ ቤቶች ካለፈው ዓመት ጀምሮ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችን እና ተቋማዊ ነጻነትን፣ ገለልተኝነትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎች ለማሻሻያ ስራው መሰረት የጣሉ እና ውጤታማ እንደነበሩ ተገለጸ፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፌደራል ፍርድ ቤቶች፣ በዳኞች አስተዳደር እና በሕገመንግሥት አጣሪ ጉባዔ የተከናወኑ ተግባራትን እና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ Read more
ዜና መግለጫ:- ፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ስለመሆናቸው ዜና መግለጫ:- ፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ስለመሆናቸው Wednesday, August 11, 2021 2007 ፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ስለመሆናቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በየዓመቱ ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በአንቀጽ 38 ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቶች የዜጎች መብቶችን የሚያስከብሩ የፍትህ ተቋማት በመሆናቸው እና የፍርድ ቤት ውሳኔና ትዕዛዝ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ወቅታዊ ምላሽ መስጠት ያስችል ዘንድ ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ ይሆናል፡፡ Read more
የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት የትውውቅና የቃለ መሐላ መርሐ-ግብር ተካሔደ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት የትውውቅና የቃለ መሐላ መርሐ-ግብር ተካሔደ Sunday, August 8, 2021 1944 የተሻሻለው የፌደራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 መጽደቁን ተከትሎ አዲስ የተደራጀው የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት የትውውቅ እና ቃለ-መሐላ የመፈጸም ሥነሥርዓት ነሐሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ተካሔደ፡፡ Read more
የዳኞች ሥልጠና ፍትሐዊና ተጠያቂነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶችን ለመገንባት እንደሚረዳ ተጠቆመ የዳኞች ሥልጠና ፍትሐዊና ተጠያቂነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶችን ለመገንባት እንደሚረዳ ተጠቆመ Saturday, August 7, 2021 1725 በፌደራል በጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዩ.ኤን.ዲፒ (UNDP) መካካል እየተተገበረ ባለው የፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት እየተካሄደ በሚገኘው የዳኞች ስልጠና ሥርዓት የዳሰሳ ጥናት ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በቤስት ዌስተርን ሆቴል ተካሔደ፡፡ Read more
የዳኞችን ዕውቀት እና ክሕሎት በማጎልበት የዳኝነት አገልግሎት አሠጣጥን ጥራት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው የዳኞችን ዕውቀት እና ክሕሎት በማጎልበት የዳኝነት አገልግሎት አሠጣጥን ጥራት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው Tuesday, August 3, 2021 1677 የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከሐምሌ 24-25 ቀን 2013 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል ተሰጠ፡፡ Read more